የሞኤንኮ ኩባንያ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤ/ጽ/ቤት የ 8100A የአጭር መልዕክት አሸናፊ የቶዮታ ሃላክስ ተሽከርካሪ ለባለ ዕድለኛው አስረከበ

ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ኩባንያችን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤ/ጽ/ቤት ግምቱ 2.2 ሚሊዮን ብር (ከቀረጥ ነፃ) የሚገመት የቶዮታ ሃላክስ ተሽከርካሪ ያበረከተውን ስጦታ ለባለ ዕድለኛው የዳውሮ ዞን ነዋሪ ለሆነው የጤና ባለሙያ ለአቶ አብርሃም ታናሹ የድርጅታችን ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ፍራንሲስ አግቦንላሆር የንግድ ሚኒስቴር አቶ መላኩ አለበል ፣የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ ሮ ሮማን ገ/ስላሴ  እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስጦታውን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤ/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አስረክበዋል፡፡

የንግድ ሚኒስትሩ ለባለ እድለኛው የእንኳን ደስያለዎት መልዕክት ያስተላላፉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የሞኤንኮ ኩባንያ ከመንግስት ጎን በመቆም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳየው የላቀ ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

የኩባንያችን የፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ሰይፈ ጌታሁን የእንኳን ደስያለዎ መልዕክት ለባለ እድለኛው ያስተላላፉ ሲሆን የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የህልውናችን ጉዳይ ነው በማለት ይህንን ሃገራዊ የልማት እንቅስቃሴ ድርጅቱ እንደሚደግፍ እና ከመንግስት ጎን እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

ታላቁ ህዳሴ ግድባችን የአንድነታችንና የሉዓላዊነታችን መገለጫ!

ጤናችን ይጠበቃል ግድባችን ይጠናቀቃል!

      

MOENCO Handover One Toyota Hilux To The Ethiopia Office Of The National Council For The Coordination Of Public Participation On The Construction Of The Dam 8100A Lottery Winner

Today June 26, 2020. Addis Ababa, Ethiopia. In support of the Government and People of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in support of the construction of the Great Ethiopian Renaissance Dam Project our Company has donated one Toyota Hilux worth about Birr 2.2 million (Duty free).

Our Company managing Director Mr.Francis Agbonlahor handed over the vehicle to the winner Ato Abreham Tanashu from Dawro Zone, Ethiopia in the presence of HE Ministry of Trade Melaku Alebel and HE W/O Roman Gebreselassie the Ethiopia Office of The National Council for the Coordination of Public Participation on The Construction of The Dam Head.

In his remarks at the event which took place at the GERD project Office in Addis Ababa, HE Minister Melaku Alebel said “Congratulations to the winner” and gave his gratitude for the donation and appreciated MOENCO for the gift.

Ato Seife Getahun, Finance Director of the company, said congratulations to the winner and said MOENCO has been playing an impactful roles in the social economic development of the country for the past 61 years since its inception; devoted to supporting government laudable programs including this historical event.

The Grand Ethiopian Renaissance Dam is our Dam and MOENCO will stand with this big Project.

#It’s my Dam#

#As we started it, we will finish it#